MMakallaTechnology
Back to blogNews

Innovation

MTMakalla Technology July 31, 2026 5 min read
Innovation

የማካላ ቴክኖዎሎጂስ እና የመንግስት ተቁዋማት ትብብር

በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተሰማርቶ 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ድርጅታችን በአርባምንጭና አከባቢው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራቱን ቀጥሎ ሰሞኑን የወረቀት ፍጆታን የሚያስቀር የአቴንዳንስና ሪፖርት አስተዳደር (ARM) ዲጂታል ስርዓት ስልጠና በመስጠት ላይ ነው::

በቴኩ ዘርፉ የላቁ ባለሙያዎችን ያቀፈው ደርጅታችን ማካላ ቴክኖሎጂስ ከጋሞ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር የወረቀት ፍጆታን የሚያስቀር የአቴንዳንስና ሪፖርት አስተዳደር (ARM) ዲጂታል ስርዓት ስልጠና ለመምሪያው ሠራተኞች እየሰጠ ይገኛል።

የጋሞ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ሀሚሶ በወቅቱ እንደገለፁት ፣ ስልጠናው ከማካላ ቴክኖሎጂስ ጋር በተፈጠረ ትብብር የሚሰጥ ሲሆን፣ የአቴንዳንስ፣ የዕረፍት፣ የመስክ ሥራ፣ የሥራ ዕቅድና የክንውን ሪፖርት አስተዳደርን ከወረቀት ነፃ በሆነ ዲጂታል ስርዓት ለማከናወን እንደሚያስችል አብራርተዋል።

የARM ዲጂታል ስርዓት ቴክኖሎጂን በማዘመንና በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል ባለፈ የወረቀት ፍጆታን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አቶ ታከለ አክለውም በመምሪያው የተጀመረው የARM ዲጂታል ስርዓት በቀጣይ በሌሎች መምሪያዎችና ተቋማት እንዲሁም መዋቅሮች እንዲስፋፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የማካላ ቴክኖዎሎጂስ ሶሉሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የARM ዲጂታል ስርዓት ከወረቀት ነፃ የሆነ ዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎት በመስጠት የተቋማትን የሥራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል።

ስርዓቱ ሠራተኞች በጣት አሻራ አቴንዳንስ እንዲፈርሙ፣ የዕረፍት ጥያቄ እንዲያቀርቡ፣ እንዲፀድቅና እንዲከታተል፣ እንዲሁም የመስክ ሥራ፣ የሥራ ዕቅድና የክንውን ሪፖርቶችን በዲጂታል መልኩ እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ሚካኤል ተስፋዬ ስልጠናው እንዲካሄድ ለተደረገላቸው ትብብር መምሪያውን አመስግነው ድርጅታቸው ዲጅታል ኢትዮጵያን ለመምጣት መንግሥት በያዘው የልማት አቅጣጫ በተፈለጉበት ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንደሚያበረክቱ አረጋግጠዋል!

Related articles